Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ለተፈናቃዮች ድጋፍ አደረገች

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ከ1 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው ዱቄትና ዘይት ለተፈናቃዮች ድጋፍ አድርጋለች፡፡

አሸባሪው የትህነግ ወራሪ ቡድን ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ ከሰሜን ወሎ ዞን ተፈናቅለው በደሴ ከተማ የመጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ነው ቤተክርስቲያኗ ድጋፍ ያደረገችው፡፡

ድጋፉን ያስረከቡት የቤተክርስቲያኗ የማኅበራዊ አገልግሎት ዘርፍ አስተባባሪ እና የባሕር ዳር ደሴ ሀገረ ሰብከት ጳጳስ ልሳነ ክርስቶስ ማቲዎስ ለተፈናቃይ ወገኖች የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

ድጋፉ የተደረገላቸው ወገኖች የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ከጎናቸው ሆነው የቻሉትን ሁሉ እየረዷቸው መሆኑን ገልጸው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ላደረገችላቸው ድጋፍ ምስጋና ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.