Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሕልውና ዘመቻው 27 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለሕልውና ዘመቻው 27 ሚሊየን ብር ለህልውና ዘመቻው ማስፈጸሚያ ድጋፍ አድርጓል።

ባንኩ ያደረገውን ድጋፍ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር እና የክልሉ መንግሥት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተረክበዋል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የባሕርዳር ዲስትሪክት ኃላፊ ስንታየሁ ልንገረው፥ የሕልውና ዘመቻው በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል ባንኩ ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል። ባንኩ ወደፊትም ድጋፍ እንደሚያደርግ ነው ያስታወቁት።

ድጋፉን የተቀበሉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አገኘሁ ተሻገር ፥ በተፈፀመብን ወረራ በወገኖቻችን ላይ ግፍ ተፈፅሞባቸዋል፤ ከፍተኛ ሀብትም ወድሟል ብለዋል።

የአማራ ሕዝብ እንደ ሕዝብ ጦርነቱን ለመመከት እየተረባረበ መሆኑንም ተናግረዋል።

ክልሉ በተለያዩ ግንባሮች ጦርነት እንደተከፈተበት የተናገሩት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ ጦርነቱን ለመመከት ተገቢው ሀብት እንደሚያስፈልግ ነው የተናገሩት።

የክልሉ ሕዝብና መላው ኢትዮጵያውያን እያደረጉት ያለው ድጋፍ የሚደነቅ መሆኑን አንስተዋል።

በችግር ጊዜ ከጎናችን ለሆኑ ሁሉ ምስጋና አቅርበው፥ ድጋፉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

አሸባሪው ኃይል ተመትቶ አሸናፊዎች እንደምንሆን እርግጠኛ ነኝ ማለታቸውንም አሚኮ ዘግቧል።

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.