Fana: At a Speed of Life!

ህልውናችንን አደጋ ላይ ለመጣል የተነሱ ቡድኖችን ለመመከት ያለልዩነት መስራት ይገባል-ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የውስጥ አንድነት አደጋ ላይ ለመጣል የተነሱ ቡድኖችን ለመመከት ያለልዩነት መስራት ይገባል ሲሉ ምሁራን ተናገሩ።

የፍልስፍና መምህሩ ዶክተር ዳኛቸው አሰፋ ፥ የለውጡ መንግስት በፈተናዎች ውስጥ ሆኖ የታላቁ የኢትዮጵያን ህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን ማሳካቱ፣ ለምዕራባውያን የማይጠመዘዝ አቅም መገንባት መቻሉ፣ ሀገር አቀፍ ምርጫን በስኬት ማካሄድ መቻሉ እንዲሁም የዲሞክራሲ ምህዳርን ለማስፋት መቻሉን በአድናቆት ጠቅሰዋል።

ሆኖም ይህ ያልተዋጠላቸው የኢትዮጵያ ጠላቶች ከውስጥና ከውጭ አብረው በሀገረ መንግስቱ ላይ አደጋ ለመጣል እየሰሩ ቢሆንም አደጋው በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እየተመከተ ነው ብለዋል።

የታሪክ መምህርና ተመራማሪው ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ላይ የስውር ደባ ሲፈፅሙ የቆዩ ቡድኖች በገሃድ ሀገር የማፍረስ ተግባር መጀመራቸውን ጠቅሰው፥ ይህ ዕኩይ ተግባራቸው የማይሳካ ነው ብለዋል።

ባለፉት አመታት አሸባሪው ቡድን ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የተኬደበት የሴረኝነት መንገድ መሆኑን ነው ያብራሩት።

ሀገረ መንግስቱን አደጋ ላይ የሚጥሉ ተግባራት እየተስተዋሉ መሆኑንም ምሁራኑ አንስተዋል።

በሀገር ህልውና ላይ የተከፈተውን አደጋ ለመመከት ህዝቡ ያሳየው አንድነትና ቁርጠኝነት የሚበረታታ እንደሆነ የጠቀሱት ምሁራኑ ፥ ይህም ለድል የሚያበቃ ተግባር ነው ሲሉ አክለዋል።

በአፈወርቅ እያዩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.