Fana: At a Speed of Life!

በከሃዲው ጄኔራል ምግበይ ሀይለ የተመራ ሃይል በማይጠብሪ ግንባር ተደመሰሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በከሃዲው ጄኔራል ምግበይ ሀይለ እየተመራ በማይጠብሪ ግንባር በደባርቅና ዳባት ወረዳዎች አዋሳኞች በጫንቅ፣ ጭና እና ወቅን አካባቢዎች የመጣው የአሸባሪው የህወሓት ቡድን ተደመሰሰ፡፡

የመከላከያ ሰራዊት መረጃ እንዳመለከተው ይህ ወራሪና ዘሪፊ የህወሓት ቡድን የእነ ወዲ ረዳን ሒሳብ የማወራረድ ስሌት ይዞ የመጣ ነው ፡፡

ከግንባሩ አዛዦች መካከል አንዱ ኮሎኔል ሀብታሙ ምህረቴ እንደገለጹት በሠራዊታችን አባላት መሪነት በግንባሩ ከተሰለፈው የወገን ሀይል ጋር በሳምንቱ ጠላት የከፈተውን ተደጋጋሚ ጥቃት በመመከትና ወደ ማጥቃት በመሸጋገር የመጣውን ጠላት ለመደምሰስና ድል ለመቀዳጀት ተችሏል፡፡

በወቅን ጭና የተሰለፈው የወገን ሀይል በወሰደው እርምጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የጁንታው ሀይል የተደመሰሰና የተማረከ ሲሆን÷ ፀረ-ታንክ፣ ዲሽቃ ፣ ብሬን፣ ላውንቸር እና ስናይፐርን ጨምሮ የተለያዩ የነፍስ ወከፍና የቡድን መሳሪያዎች ፤ ከ15 ሺህ 600 በላይ የተለያዩ ጥይቶች፣ የመገናኛ ሬዲዮና የእጅ ስልኮች እንዲሁም የብር ኖቶች ከጠላት ተማርከዋል፡፡

የአገራችን ነቀርሳ የሆነው ከሃዲው ጁንታ እንዲደመሰስና ለድሉ መገኘት የደጀኑ ህዝብ እስከ ግንባር እያደረገው ያለው ድጋፍ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ መሆኑን አዛዡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.