Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ዋና ኦዲተር ለመከላከያ ሰራዊት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ዋና ኦዲተር ለመከላከያ ሰራዊት ከ1 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ።

ለመከላከያ ሰራዊቱ የሚሰጠውን ድጋፍ ምክትል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሰረት ዳምጤ በምድር ሃይል በመገኘት ያስረከቡ ሲሆን ፥የመከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ ድጋፉን ተረክበዋል።

ምክትል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሰረት በወቅቱ እንደገለጹት፥ መከላከያ ሰራዊቱ አሸባሪውን ለመደምሰስ መስዋዕትነት እየከፈለ ይገኛል።

ስለሆነም “እኛ ደግሞ በምንችለው አቅም ድጋፍ ማድረግ ይኖርብናል” ብለዋል።

በዚህ መነሻነትም የፌዴራል ዋና ኦዲተር ሰራተኞች ከደመወዛቸው በማዋጣት ድጋፉ ማድረጋቸውን አክለዋል። በተመሳሳይ ድጋፉ በተለያየ መልኩ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

የአገር መከላከያ ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ማርታ ሊዊጂ በበኩላቸው፥ “ጠላት እኛን ሊለያይ ነበር፤ ነገር ግን ሳይሳካለት ቀርቷል” ብለዋል።

“ጁንታው አንድ አድርጎናል” ሲሉ የገለጹት ሚኒስትር ዴኤታዋ፥ አሸባሪው ህወሃት ሊበታትነን ቢፈልግም ህዝቡ ግን በአንድነት ቆሞ አገርን ለመከላከል በገንዘብ፣ በሞራል ሁሉም በየደረጃው የሚያደርገው ድጋፍ በጣም ትልቅ መሆኑን ተናግረዋል።

የተጀመረው የህልውና ዘመቻ በድል ተጠናቆ አገሪቷ ፊቷን ወደ ልማት እንድትመልስ “ዜጎች በየተሰማሩበት ሙያ ሁሉ የበኩላቸውን ሊወጡ ይገባል” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.