Fana: At a Speed of Life!

አብቁተና ሰራተኞቹ ለህልውና ዘመቻው 81 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) እና ሠራተኞቹ ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ የሚውል 81 ሚሊየን ብር አበረከቱ።

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ መኮንን የለውምወሰን ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ለዘመቻው ተቋሙ 25 ሚሊየን ብር፥ የተቋሙ ሠራተኞች ደግሞ 56 ሚሊዮን ብር ለግሰዋል።

የተቋሙ ሠራተኞች ድጋፉን ያደረጉት የአንድ ወር ደመወዛቸውን  እንደሆነም አመልክተዋል።

ሠራተኞቹ በግንባር ለተሰለፉት የጸጥታ ኃይሎች 45 ኩንታል በሶ ማዘጋጀታቸውንም ጠቅሰዋል።

ከድጋፉ በተጨማሪ የተቋሙ 159  ሠራተኞች የመንግሥትን የክተት ጥሪ ተቀብለው አሸባሪውን ህወሃት በግንባር እየተፋለሙ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

ተቋሙ ወደ ግንባር ለዘመቱት ሠራተኞቹ ሙሉ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅማቸውን ዘመቻው በድል እስኪጠናቀቅ ድረስ እንደሚሰጥ ዋና ሥራ አስፈጻሚው አረጋግጠዋል።

አሸባሪ የህወሃት ቡድኑ በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች 90 የተቋሙ ጽህፈት ቤቶች ንብረት ጉዳት ማድረሱንና ከነዚህም አንድ ጽህፈት ቤት በሙሉ በሙሉ መውደሙን አውስተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

አሸባሪውና ወራሪው የህወሃት ቡድን በአማራና አፋር ክልሎች በከፈተው ጦርነት በሰው ሕይወት፣በንብረትና በእንስሳት ላይ ጉዳት እያደረሰ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.