Fana: At a Speed of Life!

በሀረሪ ክልል ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀረሪ ክልል ለሚካሄደው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ዜጎች ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኦርዲን በድሪ ጥሪ አቀረቡ ።
በኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲወለድ የዜጎች ንቁ ተሳትፎ እጅግ ወሳኝ መሆኑን አቶ ኦርዲን በድሪ ገልጸዋል።
የ6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሂደት ነጻ፣ ፍትሐዊ፣ ዴሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ እንዲሆን የክልሉ መንግስት በቁርጠኝነት እየሠራ እንደሚገኝም ጠቁመዋል።
የክልሉን ምርጫ አስመልክቶ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በወሰነው መሰረት በሀረሪ ክልል በጀጎል ዙሪያ እና ሁንዴኔ የምርጫ ክልል በድጋሚ የመራጮች ምዝገባ ከነሀሴ 26 እስከ ጳጉሜ 5 ቀን 2013ዓ.ም ድረስ የመራጮች ምዝገባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
በቦርዱ ውሳኔ መሰረትም በሸንኮር ፣ አቦከር ፣ ሀኪም ፣ ጅንኤላ ፣ ሶፊ ፣ ድሬ ጠያራ እና በኤረር ወረዳ ነዋሪዎች ከዚህ ቀደም የወሰዱት የምርጫ ካርድ አገልግሎት ስለማይሰጥ በድጋሚ በየአካባቢው ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች በመሄድ በአዲስ ተመዝግበው የመራጭነት ካርድ መውሰድ እንዳለባቸው ገልጸዋል።
ህብረተሰብም በየአካባቢው በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎች በመገኝት ቦርዱ ባስቀመጠው የግዜ ገደብ የመራጭነት ካርድ እንዲወስዱ ጠይቀዋል።
ከክልሉ ውጪ የሚኖሩ የሀረሪ ብሔረሰቡ ተወላጆች የሚመርጡባቸው የምርጫ ጣቢያዎች አዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ፣ በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል ( አዳማ ፣ ጭሮ ፣ ኮምቦልቻ ፣ ጉርሱም ፣ ፈዲስ ፣ ደደር እና ሃሮማያ) ፣ ድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር ፣ እና በሶማሌ ብሔራዊ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተቀመጠው የግዜ ገደብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ዴሞክራሲያዊ መብታችሁን በአግባቡ ልትጠወሙበት ይገባል በማለት ገልጸዋል።
የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን ፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ ፤ ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።
በተጨማሪ ሁሉም አካላት ምርጫው በታቀደለት የጊዜ ገደብ ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
May be an image of 1 person
0
People Reached
0
Engagements
Distribution Score
Boost Post
Like

Comment
Share
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.