Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል ባደረሰው ጥቃት ተጎጅዎች ለሰብአዊ ቀዉስ ተዳርገዋል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስምንት ልጆች እናት የሆኑት ወይዘሮ አሚናት ይማም የሽብር ቡድኑ በከልዋን ወረዳ አካባቢ በፈጸመዉ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጥቃት በርካቶች እንደሞቱ ገልፀዋል፡፡
ህውሓት የአካባቢዉ ኗሪዎች ላይ ካስከተለዉ ዘግናኝ ህልፈት ባሻገር ቤት ንብረታቸዉ ላይ ጉዳት ማድረሱንም ወይዘሮ አሚናት ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ አስረድተዋል፡፡
ቡድኑ በፈጸመዉ ጥቃት ሁለት ልጆቻቸዉን ያጡት አቶ አህመድ ከድር ጥቃቱ የቡድኑን ኢሰብአዊ ድርጊት በግልጽ ያሳየ እና የቡድኑ አረመኔያዊ ጠባይ የተገለፀበት ነው ብለዋል፡፡
ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በነበረዉ ቆይታ የጁንታዉን ሃይል ጥቃት ተከትሎ በርካታ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸዉ ተፈናቅለዉ እና በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን መመልከት ችሏል ፡፡
ጋሊኮማ ቀበሌን በመሰሉ አካባቢዎች በተፈጸመዉ ጥቃት የህዝብ መገልገያ የሆኑና በህዝብ ሃብት የተገነቡ ትምህርት ቤቶች፣ የጤና ተቋማት እና ሌሎች መሰረተ ልማቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
ተጎጅዎች እየተደረገላቸዉ ያለዉ ድጋፍ በቂ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡
የሽብር ቡድኑን ጥቃት ተከትሎ በክልሉ ከ1መቶሺ በላይ ዜጎች ከመኖሪያ ቀያቸዉ እንደተፈናቀሉ ከክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡
ለተጎጅዎች የሚደረጉ ድጋፎች ይኑሩ እንጅ ካለዉ ችግር አንጻር ድጋፎች በቂ እንዳልሆኑ በጽህፈት ቤቱ የድጋፍ ሰጭ አስተባባሪ አቶ ማህር አሊ ገልፀዋል፡፡
የክልሉ መንግስት ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለተጎጅዎች ለመድረስ እየተሰራ እንደሆነም አብራርተዋል ፡፡
አሁንም የሚስተዋለዉን የጊዜያዊ መጠለያ ዳስ ለማስተካከል ተመሳሳይ ስራዎች እየተከናወኑ እንደሚገኝ የጠቆሙት አስተባባሪዉ ለተጎጅዎች የወገን ድጋፍ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል፡፡
በአወል አበራ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.