Fana: At a Speed of Life!

አንጋፋው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ በድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ።

“ተማር ልጄ” በሚለው ዘመን ተሻጋሪ ዘፈኑ የብዙዎችን ቀልብ የማረከው ድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ነሐሴ 27፣2013 እኩለ ሌሊት በድንገት ማረፉ ነው የታወቀው።

“ተማር ልጄ ሌት ፀሀይ ነው ላልተማረ ሰው ግን ቀኑ ጨለማ ነው…” እያለ ሚሊየኖችን በዜማው መክሯል።

አንጋፋዉ ሙዚቀኛ አለማየሁ እሸቴ በሚጫወታቸው የሙዚቃ ስራዎቹ ‘ኤልቪስ ፕሪስሊ’ የሚል ቅፅል ስምም ተሰጥቶት ነበር።

ስቀሽ አታስቂኝ” ፣ ” እንደ አሞራ ክንፍ አውጥቼ ልብረራ”፣ ” ማን ይሆን ትልቅ ሰው” ፣ ” ምሽቱ ደመቀ”፣ “አዲስ አበባ ቤቴ” ፣ “የወይን ሃረጊቱ” ፣ “የሰው ቤት የሰው ነው”፣ “ደንየው ደነባ”፤ “ትማርኪያለሽ”፣ “ወልደሽ ተኪ እናቴ” እና ” ተማር ልጄ” ከአለማየሁ እሸቴ ሙዚቃዎች በዋናነት የሚጠቀሱለት ናቸው።

የድምፃዊው ድንገተኛ ህልፈት ተከትሎ ብሔራዊ ቴአትርን ጨምሮ አድናቂዎቹ ሀዘናቸውን እየገለፁ ይገኛል።

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በድምፃዊው ህልፈት የተሰማውን ሀዘን አየገለፀ ለቤተሰቦቹ፣ ወዳጅ ዘመዶቹና አድናቂዎቹ መፅናናትን ይመኛል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.