Fana: At a Speed of Life!

የሽብርተኞቹ ህወሓትና ሸኔ ጥምረት ሃገር የማፍረስ እኩይ ስምምነት ነው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪዎቹ ህወሓትና ሸኔ ጥምረት ድሮም የነበረ ሃገር የማፍረስ እኩይ ስምምነት መሆኑን የምስራቅ ሐረርጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሁሴን ፈይሶ ገለጹ።

አቶ ሁሴን ፈይሶ እንደተናገሩት፥ አሁን በግላጭ የተናሩት ሃቅ ህዝብም መንግስትም የሚያውቁት ቢሆንም የሸኔ ሽብር ቡድን ከህወሓት ጋር ያደረገው ያልተቀደሰ ጋብቻ ከኦሮሞ ህዝብ ጋር ለአንድና ለመጨረሻ ጊዜ ፍቺ ያደረገበት ስምምነት ተደርጎ ሊወሰድ ይገባዋል፡፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ለጀግናው መከላከያ ሰራዊት እና ለሌሎች የጸጥታ ሃይሎች ድጋፍ የሚውል 45 ሚሊየን ብር ቃል የተገባ ሲሆን÷ እስካሁን 28 ሚሊየን ብር መሰብሰቡን ገልጸዋል።

የዞኑ ሴቶች ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሆነ ደረቅ ሬሽን አዘጋጅተው መላካቸውን የገለጹትአቶ ሁሴን፥ 6 ሺህ ወጣቶችንና ሚሊሻዎች ወደ መከላከያ እንዲቀላቀሉ ተመርቀው መሸኘታቸውንም ጠቁመዋል።

የምስራቅ ሐረርጌ ዞን አስተዳደርና ጸጥታ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አህመድናጅ አቡበከር÷ የህወሓትንም ሆነ የሸኔ ሰርጎ ገቦችን ህብረተሰቡ በንቃት እየተከታተለ በመሆኑ እስከ አሁን ድረስ 60 የሚደርሱ ሰርጎ ገቦችን በቁጥጥር ስር መዋላቸውን አስረድተዋል።

በዞኑ በአሁኑ ሰዓት ፀጥታው፣ ሰላምና ልማቱ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማስታወቃቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.