Fana: At a Speed of Life!

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በ195 ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን ፕሮጄክቶች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በ195 ሚሊየን ብር ያስገነባቸውን የኢንተርኔት ማስፉፊያና የመረጃ ማዕከል ስራዎች አስመረቀ፡፡
 
የላቀ የዩኒቨርሲቲዎች ትሰስር ለዘላቂ ልማት! በሚል መሪ ቃል ትምህርታዊ ዓውደ ርዕይ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው፡፡
 
በዓውደ ርዕዩ የተለያዩ የሳይንስ ግኝቶችን ጨምሮ በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ የቴክኖሎጂ ስራዎች ቀርበዋል።
 
ዓውደ ርዕዩ በአካባቢው የንዱን ማህበረሰብ እና ኢንዱስትሪውን ለማስተሳሰር ያለመ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዑባህ አደም ተናግረዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም መድረኩ ለዩኒቨርሲቲዎች የውስጥ ትስስር ያለው ሚና የላቀ መሆኑን ነው የገለጹት፡፡
 
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ደኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ በበኩላቸው÷ባለፋት ሶስት ዓመታት የዩኒቨርሲቲዎች ሪፎርም በልየታ ላይ የተመሠረተ እንደነበር አንስተዋል፡፡
 
በዚህ መርህ መሠረት ለኢዱስትሪው ድጋፍ እንዲሰጥ በማሰብ በአፕላይድ ዩኒቨርሲቲነት የተመደበው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሀገሪቱን ብልጽግና ለማሳካት ከፍተኛ ሚና መጫወት አለባቸው ብለዋል።
 
የድሬዳዋ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጀዋር÷ ዩኒቨርስቲው ከተማዋን ከኢንዱስትሪ ጋር ለማስተሳሰር እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡
 
ከቦታ ጥበት ጋር በተያያዘ ያለበትን ችግር ለመፍታት ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አመራሮች ጋር በመነጋገር ከመግባባት ላይ መደረሱን ነው የገለጹት፡፡
 
በዓውደ ርዕዩ ከ40 ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ የቢዝነስ ልማት ዳይሬክተሮች እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡
 
በእዮናዳብ አንዱዓለም
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.