Fana: At a Speed of Life!

በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማዕከል ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ሼክ ሀሰን የበሬ ሪፈራል ሆስፒታል የኩላሊት እጥበት ማዕከልን መርቀው ከፈቱ፡

ማዕከሉ በ27 ሚልየን ብር ወጪ የተገነባ ሲሆን÷ወጪው በዲያስፖራ ወጣቶች በራስ ተነሳሽነት፣ ከህዝቡ በተሰበሰበ እንዲሁም በክልሉ መንግሥት የተሸፈነ ነው፡፡

ማዕከሉ 10 ማሽኖች የተገጠሙለትና በቀን ለ20 ሰው የኩላሊት እጥበት አገልግሎት መስጠት እንደሚችል የክልሉ ጤና ቢሮ ምክትል ሀላፊ ዶክተር ሸርማርኬ ሸሪፍ ገልፀዋል።

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ በምረቃ ሥነ ስርአቱ ላይ ይህንን ሀሳብ ላመጡት ወጣቶች ምስጋና አቅርበው የክልሉ መንግስት ለህዝቡ ፋይዳ ያላቸው ሀሳቦችን የሚያመጡ ወጣቶችን ያግዛል ማለታቸውን ከሶማሌ ክልል መገናኛ ብዙሃን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

መንግሥት እና ህዝብ በተቀናጀ መልኩ ከሰራ መሰል ማዕከሎች ይገነባሉ ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ ለኩላሊት እጥበት ማዕከሉ አስፈላጊውን እገዛና ድጋፍ በማድረግ፣ ከኩላሊት ጋር ተያይዞ ህዝባችን ወደ ውጭ ሀገራት የሚያደረገውን ጉዞ ለማስቀረት ይሰራል ብለዋል ፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.