Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በአንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በአንጋፋው ድምጻዊ አለማየሁ እሸቴ ህልፈት የተሰማቸውን ሃዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቷ በመልዕክታቸውም÷ ሃገራችን ካፈራቻቸው ታላላቅ ድምጻውያን አንዱ በሆነው በአለማየሁ እሸቴ ዜና እረፍት እጅግ አዝኛለሁ ብለዋል፡፡

‘‘የአለማየሁ ዘመን ተሻጋሪ እና ቁም ነገር አዘል ግጥም እና ዜማዎቹ በኢትዮጵያዊያን ልብ ውስጥ ለዘለዓለም ይኖራሉ’’ ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ለቤተሰቦቹ እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም መጽናናትን ተመኝተዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.