Fana: At a Speed of Life!

ባለፈው በጀት ዓመት 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚገመት የኮንትሮባንድ ገቢና ወጪ ንብረት ተይዟል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ በ2013 በጀት ዓመት በተሰራ ስራ 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚገመት ገቢና ወጪ ንብረት መያዝ መቻሉን የፌዴራል ፖሊስ ገለጸ።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የ2013 በጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም ግምገማ እያካሄደ ሲሆን÷በዚህም በበጀት ዓመቱ ያከናወናቸውን ስራዎች ሪፖርት በማቅረብ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

በሪፖርቱ በዓመቱ በዋናነት በግንባር አካባቢዎች አሸባሪው የህውሓት ቡድን ላይ በተወሰዱ እርምጃዎች ዙሪያ ማብራሪያ ተሰትጥቷል።

በዚህም ከወትሮው በተለየ መልኩ የክልል ልዩ ሃይል አባላትን በማስተባበር የተሰራው ስራ ጥሩ ውጤት ያስገኘና አሸባሪው ቡድን ሲሰራ የቆየውን የመከፋፈል ሴራ ያፈረሰ መሆኑ ተነስቷል።

በተጨማሪም በዓመቱ በተደረገ ክትትልና ጥብቅ ፍተሻ በርካታ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ መያዙን በሪፖርቱ ተመላክቷል።

በኮንትሮባንድ እንቅስቃሴ ላይ በተሰራ ስራም 3 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር የሚገመት ገቢና ወጪ ንብረት መያዙ ነው የተገለተው።

የፌደራል ፖሊስ በ6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ወቅት ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ስራ መሰራቱ ተጠቁሟል።

የወንጀል ምርመራ ስራም ተጠናክሮ መቀጠሉንና በዓመቱ ከፍተኛ የወንጀል ምርመራዎችን ማድረግ መቻሉ ተገልጿል።

በዘመን በየነ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.