Fana: At a Speed of Life!

አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ታስበው ይውላሉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተለያዩ ሁነቶች ታስበው እንደሚውሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳድር የ2014 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለሚያከናውናቸው ተግበራት በመዲናዋ ቀናቶቹ ታስበው እንደሚውሉ ተሰምቷል፡፡

በዚህም ‘’በከተማዋ በባለፈው ዓመት የታዩ ህዝባዊ አንድነትን፣ ሰለማዊ ምርጫ መካሄድን፣ የ’ይቻላል’ መንፈስ ማደግን፣ ሰላም የማስከበር ስራን ስኬት፣ የፕሮጀክቶቻችን በአለም መድረክ እውቅና ማግኘትን እና የመሳሰሉትን የበርካታ ድል ባለቤት መሆናችንን መነሻ በማድረግ አምስቱ የጳጉሜ ቀናት በተላዩ ሁነቶች ታስበው ይውላሉ’’ ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

ጳጉሜ 1 የኢትዮጵያዊነት ቀን፣ ጳጉሜ 2 የአገልጋይነት ቀን፣ ጳጉሜ 3 የመልካምነት ቀን፣ ጳጉሜ 4 የጀግንነት እና ጳጉሜ 5 የድል ቃልኪዳን ብስራት ቀን ሆኖ ታስቦ ይውላል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.