Fana: At a Speed of Life!

ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል ይፋ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው አገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው አካባቢዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰዓትና የጋዜጣ አምድ ድልድል በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓት ይፋ ተደረገ፡፡

ድልድሉን የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመተባበር ነው ይፋ ያደረገው፡፡

የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ወይዘሪት ሶሊያና ሽመልስ 6ኛው አገራዊ ምርጫ ባልተካሄደባቸው በደቡብ፣ ሶማሌና ሃረሪ ክልሎች መስከረም 20 ቀን 2014 ዓ.ም ምርጫ እንደሚካሄድ በዕጣ አወጣጥ ስነ ስርዓቱ ወቅት አስታውቀዋል፡፡

ባለስልጣኑ ለ22 የፖለቲካ ፓርቲዎችና ለ106 ዕጩ የግል ተወዳዳሪዎች በ3 ሬዲዮ፣ በ4 ቴሌቪዥንና በ2 የጋዜጣ አምድ ላይ ድልድል አድርጓል፡፡

ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተመደበው የአየር ስዓት በቴሌቪዥን 2 ሺህ 340 ደቂቃ፣ በሬዲዮ 1 ሺህ 920 ደቂቃ እና በጋዜጣ 45 ዓምድ ሲሆን ለግል ዕጩ ተወዳዳሪዎች ደግሞ በቴሌቪዥን 1 ሺህ 590 ደቂቃ ና በሬዲዮ 1 ሺህ 590 ደቂቃ መሆኑን ታውቋል፡፡

የቅስቀሳ ፕሮግራሙ በተጠቀሱት ክልሎች ላይ ከጳጉሜ 2 ቀን 2013 ዓ.ም እስከ መስከረም 14 ቀን 2014 ዓ.ም እንደሚከናወን ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.