Fana: At a Speed of Life!

የውጭም ይሁን የውስጥ ጠላት የኢትዮጵያን ሉአላዊነት እንዲደፍር አንፈቅድለትም-አባ ገዳዎች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ ) “የውጭም ይሁን የውስጥ ጠላት የኢትዮጵያን ክብርና ሉአላዊነት እንዲደፍር በፍፁም አንፈቅድለትም” ሲሉ የሐይማኖት አባቶችና አባ ገዳዎች ተናገሩ።
የኦሮሚያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤና አባ ገዳዎች በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ላይ እየተወያዩ ነው።
በውይይቱ ላይ አባ ገዳ አሊይ መሐመድ “አሸባሪው ህወሓት ባለፉት ዓመታት በህዝባችን ላይ ተቆጥሮ የማያልቅ በደል ፈጽሟል” ብለዋል።
አሁንም ኢትዮጵያን ለመበታተን ቆርጦ በመነሳቱ ሁሉም በአንድነት በመቆም ዓላማውን ማክሸፍ እንዳለበት አስገንዝበዋል።
ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ጥምረት የሚፈጥርም ሆነ የሚተባበር ማንኛውም አካል የህዝብ ጠላት መሆኑንም ገልጸዋል።
“የውጭም ይሁን የውስጥ ጠላት በፍጹም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ይቅርና እንዲዳፈር አንፈቅድም” ያሉት አባ ገዳ አሊይ፤ “አሸባሪውን ቡድን በጋራ በመመከት የኢትዮጵያን ክብርና ሉአላዊነት እናስከብራለን” ብለዋል።
ከውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል ሼህ መሀመድ ሳኒ እንዳሉት፤ አሸባሪው ህወሐት በሃይማኖት ግልፅ ጣልቃ በመግባትና በማፈን ብዙ በደል ፈፅሟል።
“አሁንም ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ በመሆኑ ያለምንም ልዩነት በአንድነት ቆመን በመመከት ማስወገድ አለብን” ብለዋል።
አሸባሪው ሸኔ ከአሸባሪው ህወሓት ጋር ጥምረት በመፍጠር በህዝብ ላይ ይበልጥ የጭካኔ ተግባር ለመፈፀም መዘጋጀቱን በግልፅ ያሳየበት አጋጣሚ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
“አገር ከሌለ ምንም ነገር መስራት አይቻልም፤ ከምንም በላይ አገር መቅደም ስላለበት ለአገራችን በጋራ ዘብ መሆን አለብን” ያሉት ደግሞ ሌላኛው የመድረኩ ተሳታፊ ሃጂ ሻፊ ያሲን ናቸው፡
“ኢትዮጵያዊያን በምንም ሳንከፋፈል አገራችንን በጋራ ሆነን ከጠላት የምንጠብቅበት አጋጣሚ አሁን ነው” ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.