Fana: At a Speed of Life!

ቀይ መስቀል ማሕበር ለአፋር ዱብቲ ሆስፒታል ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ማሕበር ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር ጋር በመተባበር ለአፋር ዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል የቁሳቁስና የመድሃኒቶች ድጋፍ ማድረጉን የማሕበሩ የአፋር ክልል ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሃላፊ አሊ ሶሃሊህ ገለፁ፡፡

የዱብቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶክተር መሐመድ የሱፍ በበኩላቸው÷ ሆስፒታሉ ለ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን የአካባቢው ነዋሪዎች አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በክልሉ እያደረሰ ባለው ጥቃት ወደ ሆስፒታሉ የሚመጡ ታካሚዎች ቁጥር መጨመሩን የገለጹት ስራ አስኪያጁ÷ በዚህም የመድሐኒትና የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ እጥረት ማጋጠሙን ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርም የሆስፒታሉን ችግር በማጤን 5ሚሊየን ብር የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና መድሃኒትድጋፍ በማድረጉ አመስግነው÷ ሌሎች ተራድዖ ድርጅቶችም ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

የአፋር ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አሚና ሲኮ በድጋፍ ርክክቡ ወቅት የተገኙ ሲሆን÷ ቀይ መስቀል ማህበር በክልሉ ያሉ ችግሮችን በቅርበት በመከታተል ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡

የአፋር ቅርንጫፍ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ኃላፊም ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

በጌታሰው የሽዋስ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.