Fana: At a Speed of Life!

ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረ የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል ተደመሰሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ከሱዳን በአልምሃል ሰርጎ ለመግባት የሞከረው የጁንታው ቅጥረኛ ሃይል በጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት ተደምስሷል፡፡

በዚህ ተልዕኮ የሕዳሴውን ግድብ ግንባታ ለማደናቀፍ በሱዳን ሰርጎ ለመግባት የሞከሩ 50 የሽብር መልዕክተኞችና የጁንታው ቅጥረኞች ሲደመሰሱ ከ70 በላይ የሚሆት ደግሞ ቆስለዋል፡፡

የመተከል ዞን የተቀናጀ ግብረ ሃይል ኮማንድ ፖስት የኦፕሬሽን ዘርፍ አሰተባባሪ ኮ/ል ሰይፈ ኢንጊ÷ ቅጥረኛው የተለያዩ ፀረ ሰው እና ፀረ ተሽከርካሪ ፈንጂዎችን ለማጥመድ የሞከረ ቢሆንም መቋቋም ተስኖት ተበታትኗል ብለዋል፡፡

ጠላት አሳቻ ሰዓት ጠብቆ አካባቢውን ለማተራመስ ቢንቀሳቀስም የጠላትን እንቅስቃሴ ከመነሻው በንቃት ሲከታተሉ የነበሩት የመከላከያ ሰራዊቱ ክፍሎች ተቀናጅተው እርምጃ እንደወሰዱበት ነው የገለጹት ፡፡

የጠላት ሃይል የቻለውን ያህል ለመከላከል ቢሞክርም በጀግናው ሰራዊት የበላይነት ተወስዶበት የተረፈው ሃይል አግሬ አውጪኝ ብሎ መፈርጠጡን ኮ/ል ሰይፈ ተናግረዋል፡፡

የጥፋት ሃይሉ ሲጠቀምባቸው እና ለእኩይ ስራው ሲያዘጋጃቸው የነበሩ ቀላል እና ከባድ የቡድን መሳሪያዎች ፣ ፈንጂዎች የወደሙ ሲሆን÷ የተቀሩት በጀግናው ሰራዊት ቁጥጥር ስር ገብተዋል ነው ያሉት፡፡

አሸባሪው የህወሓት ቡድን በግንባር ድል አልቀና ሲለው አብዛኝው ጦር ወደ ሰሜኑ ክፍል አቅንቷል በሚል ከታሪካዊ ጠላቶች ተቀናጅቶ የህዳሴ ግድቡን ስራ ለማስተጓጎልና ለማጥቃት ቢሞክርም እንዳልተሳካለት ነው የተናገሩት፡፡

በአሁኑ ስዓት በአካባቢው ጀግናው የመከላከያ ሃይል፣ እግረኛና ሜካናይዝድ ክፍለጦሮች እንዲሁም የክልል ልዩ ሐይሎች አስፈላጊውን ዝግጁነት በማረጋገጥ ግዳጃቸውን እየፈፀሙ እንደሚገኙ ኮ/ል ሰይፈ መገለጻቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.