Fana: At a Speed of Life!

በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን 18 ቢሊየን ችግኝ ተተክሏል

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እስካሁን 18 ቢሊየን ችግኝ መትከል መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊትር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ÷የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በፈረንጆቹ 2019 ላይ በ4 ዓመታት ውስጥ 20 ቢሊየን ችግኞን ለመትከል ታቅዶ መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡
በመርሃ ግብሩ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ በአጠቃላይ 18 ቢሊየን ችግኝ መትከል መቻሉን ነው የገለጹት፡፡
ይህም በእያንዳንዱ ዓመት ከታቀደው በላይ ማሳካት መቻሉን ያሳያል ነው ያሉት፡፡

በመርሃ ግብሩ የተመዘገበውን ውጤት በቀጣይ የህዝቦችን አንደነት እና የጋራ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ረገድ እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ለመድገም በቅንጅት እንደሚሰራም ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.