Fana: At a Speed of Life!

የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን መደገፍ የሚያስችል የትብብር ስምምነት ተፈረመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማትን መደገፍ የሚያስችል የትብብር ስምምነት በኢትዮጵያና በጀርመን መካከል ተፈረመ።

ስምምነቱ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማእቀፍ የኢትዮጵያ የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እና ፖሊሲን ለመደገፍ የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

የኢትዮጵያ ዲጂታል ኢኮኖሚን ለግሉ ዘርፍ የተመቸ ማድረግ እና የግሉ ዘርፍም ተገቢውን አስተዋጽኦ እንዲያረግ ማስቻል የሁለቱም ሀገራት ፍላጎት መሆኑ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በተለይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች በዲጂታል ኢኮኖሚው ውስጥ በሚገባ እንዲሳተፉ ማስቻል ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠው መጠቆሙን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ስምምነቱን በጀርመን መንግሥት በኩል የጀርመን የኢኮኖሚ ጉዳዮች እና ኢነርጂ ምክትል ሚኒስትር ቫንደርቪትዝ ሲፈርሙ÷ በኢትዮጵያ በኩል ደግሞ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርን በመወከል በጀርመን የኢፌዴሪ ባለ ሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን ፈርመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.