Fana: At a Speed of Life!

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ ተወሰነ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የዋጋ ንረት በህብረተሰቡ ላይ የሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስ ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና ሩዝ ከቀረጥና ታክስ ነጻ እንዲሆኑ መወሰኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ኢዮብ ተካልኝ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፥ ወሳኝ በሆኑ ሸቀጦች ላይ ቀረጥና ታክስ ማሻሻያ መደረጉን ተናግረዋል።

በመግለጫቸውም ፖስታ እና ማካሮኒ የጉምሩክ ቀረጡ እንዳለ ሆኖ ተጨማሪ እሴት ታክስ እንደተነሳላቸውም ነው የተናገሩት።

ስንዴ፣ ዘይት፣ ስኳር እና የሩዝ ምርቶች ከውጭም ሆነ ከሃገር ውስጥ ግዥ ሲፈጸም ከማንኛውም ቀረጥ ነጻ እንዲሆኑ ተወስኗልም ብለዋል በመግለጫቸው።

ከዚህ ባለፈም በዶሮ እንቁላል ላይ የነበረው ተጨማሪ እሴት ታክስ ፍላጎት እና አቅርቦት እስከሚጣጣም ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ ሆኖ ለገበያ እንዲቀርብ ተወስኗልም ነው ያሉት።

ይህም ከዛሬ ጀምሮ ለሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች እና አስፈጻሚ አካላት መመሪያ መተላለፉን አንስተዋል።

ሚኒስትር ዲኤታው በመግለጫቸው የፍራንኮ ቫሉታ ፈቃድ በመራዘሙ ምርት ማስገባት የጀመሩ መቀጠል እንደሚችሉም ጠቁመዋል።

በትእግስት አብረሃም እና ፍሬህይወት ሰፊው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.