Fana: At a Speed of Life!

የአሶሳ ከተማ ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሠልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአሶሳ ከተማ የተለያዩ የሴት አደረጃጀቶችና የከተማው ሴቶች ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የድጋፍ ሠልፍ ዛሬ አካሂደዋል።

የከተማው ሴቶች ባካሄዱት ሠልፍ አሸባሪውን የህወሓትን ቡድን የሚያወግዙና ለሃገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፋቸውን የሚያረጋግጡ የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል፡፡

በድጋፍ ሠልፋ ላይ የክልሉ ሴቶች ሊግ አባላትን ጨምሮ፣ ከአሶሳ ከተማ አስተዳደር ከአሶሳ ወረዳ የተውጣጡ ሴቶች የተሳተፉ ሲሆን አሸባሪው ቡድን በሴቶችና ሕጻናት ላይ የሚያደርሰውን ጥቃት እና ጅምላ ጭፍጨፋ በጽኑ እንደሚያወግዙ ገልጸዋል።

በድጋፍ ሠልፉ ላይ የተገኙት የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኢስሃቅ አብዱልቃድር የህዳሴ ግድብ ሙሌት በሠላም መጠናቀቅ ጋር ተያይዞ ውድቀታችን የሚመኙ የውጭና የውስጥ ተላላኪዎች የጀመሩትን የጥፋት ሴራ ለማክሸፍ ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከዳር ተነስተዋል ማለታቸውን ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.