Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በወቅታዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማዕከል የምርጫ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ዛዲግ አብርሃ የትግራይ ህዝብ ለኢትዮጵያ ዋጋ የከፈለ ህዝብ መሆኑን ገልጸዋል።

ይሁን እንጅ አሸባሪው ህወሓት በውሸት ፕሮፓጋንዳ ለጦርነት በመማገድ የጥፋት ስራውን እያከናወነ እንደሚገኝም ነው የገለጹት።

የተጀመረውን ለውጥ ለማስቆም ሃይል የሌለው ጁንታው የህወሓት ቡድን የጥፋት ሴራውን በመገንዘብ÷ በተለይም ምሁራን ኢትዮጵያን ለማተራመስ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እውነታን ከማስረዳት አንጻር እንደ ትዊተር ባሉ የተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ በሚደረጉ ዘመቻዎች ላይ እውነታውን በማሳወቅ ረገድ የድርሻቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል ።

በአዲስ አበባ ከተማ በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የሱፐርቪዥን ጥናትና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳዊት የሺጥላ÷ መንግስት ህግን ለማስከበር ተገፍቶ የገባበት ጦርነት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ምሁራን በጦርነቱ የሚደርሱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥፋቶችን ሊቀንስ በሚችል መልኩ ምክክሮች እና ጥናቶችን ማድረግ እንደሚገባቸው ጠቅሰዋል ።

ከውጭም ከውስጥም የተደቀነውን አደጋ በመከላከል ረገድም ሰላሟ የተጠበቀ፣ የበለጸገች፣ ጠንካራ ኢትዮጵያን ለልጆቿ ለማውረስ ሁሉም የድርሻውን መወጣት ይገባዋልም ነው ያሉት።

የመጣው ለውጥ ለምሁራን ጥሩ አጋጣሚ የፈጠረ በመሆኑ ለሃገር ጠቃሚ የሆኑ ሥራዎችን መሥራት አለባቸው ሲሉ የገለጹት ምሁራኑ÷ “ኢትዮጵያ ስትኖር ነው ሁላችን መኖር የምንችለው” ስለሆነም የሀገርና የተቋማት ግንባታ እንዲሁም የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ከመፍጠር አኳያ የበኩላቸውን ሚና እንደሚወጡ ገልጸዋል ።

ኢትዮጵያ የባለብዙ ሃብት ባለቤት መሆኗን የጠቀሱት ምሁራን÷ ሰፋፊ የጥናት እና ምርምር ላይ በመስራት ኢትዮጵያ የዚህ ሃብት ተጠቃሚ በመሆን ከድህነት እንድትላቀቅ ማድረግ እንደሚቻል ማንሳታቸውን ከአዲስ አበባ ብልጽግና ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.