Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ሬድዋን ከሶማሌላንድ ፕሬዚዳንትጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ከሶማሌላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
 
በውይይታቸውም በድንበር አካባቢ ያለውን የጸጥታ እና ኤምግሬሽን ጉዳዮች እንዲሁም የባህል ልውውጥን ማሳደግ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነቱን ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸው ነው የተገለጸው፡፡

 
አምባሳደር ሬድዋን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሊበን ዩሱፍ ጋር ባደረጉት ውይይት የኮቪድ-19 ገደቦችን ታሳቢ ባደረገ መልኩ በውጫሌ ድንበር የኢሚግሬሽን አገልግሎት ዳግም በሚጀመርበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።
 
ለሁለት ቀናት ይፋዊ የሥራ ጉብኝት በትላንትናው ዕለት ሶማሌላንድ የገቡት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ ከሶማሌላንድ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን የበርበራ ወደብ ኮሪደርን መጎብኘታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
ከሳሂል ክልል አስተዳዳሪ አህመድ ኦስማን እና ከበርበራ ከንቲባ አብዲሻኩር ሞሐሙድ ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ሶማሊላንድ የኢትዮጵያ የኤክስፖርት ምርቶች መዳረሻ የመሆን አቅም ያላት መሆኑን ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ የበርበራ ወደብ ኮሪደርን በመጠቀም ከሶማሊላንድ ጋር ያላትን የኢንቨስትመንት እና የቱሪዝም ተሳትፎዋን በማሳደግ የኢኮኖሚ ትስስሯን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ የማድረግ ፍላጎት እንዳላት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ገልጸዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.