Fana: At a Speed of Life!

በወርቅ አምባ፣ ቡና ሜዳ እና ዝንጆሮ አፋፍ አካባቢዎች ህወሓት ያሰማራቸው የጥፋት ሃይሎች ተደመሰሱ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በማይጠብሪ ግንባር ለማጥቃት የመጣው የከሀዲው ኮ/ል ኪሮስ ገ/ኪዳን ክፍለጦር እሱን ጨምሮ በወርቅ አምባ፣ ቡና ሜዳ እና ዝንጆሮ አፋፍ አካባቢዎች ያሰማራቸው የጥፋት መልዕክተኞቹ ተደምስሰዋል፡፡
ትላንት ለሊት 10 ሰዓት እና ዛሬ ረፋድ ላይ በከሀዲው ኮ/ል ኪሮስ ገ/ኪዳን የሚመራው ክ/ጦር ሙሉ በሙሉ ሲደመሰስ እሱን ጨምሮ የጁንታው አመራሮች ከሆኑት መካከል ሌ/ኮ ገ/ፃዲቅ ምሩፅ መደምሰሱን የግንባሩ አመራሮች አረጋግጠዋል፡፡
 
በተደረጉት አውደ ውጊያዎች አሸባሪው የህውሓት ቡድን ሲጠቀምበት የነበረው ከ27 ሺ በላይ የተለያዩ ጥይቶች፣ ዲሽቃ፣ ብሬን ፣ ስናይፐር፣ መገናኛ ሬድዮ እንዲሁም ህዝብን መደናገሪያ ሊጠቀምበት የነበረውን የሀሰት የአማራ ክልል ማህተም መማረክ ተችሏል ብለዋል፡፡
 
አዛዥ እንደገለፁት ፣ ይህ ድል በምዕራብ ዕዝ የሠራዊት አባላት፣ በአማራ ልዩ ኃይል እና ሚሊሺያ እንዲሁም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል በጋራ የተገኘ ነው ፡፡
 
በአካባቢው የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከሠራዊቱ ጎን በመሆን አሁን በግንባር ተሰልፈው የሚጠበቅባቸውን እየተወጡ እንደሚገኙ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.