Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በአለም አቀፍ ደረጃ በሽብር የሚያስፈርጁ ሁሉንም ወንጀሎች ፈጽሟል – የህግ ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አሸባሪው ህወሓት በአለም በሽብርተኝነት የሚያስፈርጁ ሁሉንም ወንጀሎች መፈፀሙን የህግ ምሁራን ገለፁ።

በሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የህግ መምህር የሆኑት መምህር መሀመድ ሰይድ ÷በስልጣን በቆየበት ዘመኑ ከባድ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈፅም የቆየው ትህነግ አሁን እየፈጸማቸው ያሉ ግፎች በአለም አቀፍ ወንጀል የሚፈረጁ መሆናቸውን ገልፀዋል።

በዩኒቨርሲቲው ሌላው የህግ መምህር አቶ ምንዳ ግርማ በበኩላቸው ÷በአለም አቀፍ ወንጀለኝነት ከሚያስጠይቁ አራት ወንጀሎች ትህነግ ሶስቱን ማለትም ዘር የማጥፋት፣በሰው ልጅ ክብር የሚፈፀም ወንጀልና የጦር ወንጀሎችን መፈፀሙን ተናግረዋል።

ትህነግ የፈፀማቸው ወንጀሎችም በአለም አቀፍ ወንጀለኝነት ብቻ ሳይሆን በአለም አቀፍ ሽብርተኝነት የሚያስፈርጁ መሆናቸውንም ምሁራኑ ገልፀዋል።

ሆን ብሎ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት መፈፀሙ ፣የፈጸማቸው ወንጀሎች በአለም አቀፍ ህግ ህገ ወጥ መሆናቸውና ሁሉንም ወንጀሎች ሆን ብሎ መፈፀሙ በአለም አቀፍ ሽብርተኝነት እንዲፈረጅ የሚያደርጉት መሆኑንም የህግ ምሁራን ተናግረዋል።

በንፁሃንና በተቋማት ላይ ጥቃት መፈፀሙና ጥቃት ያደረሰው ለፖለቲካ አላማ መሆኑ ትህነግን በአለም አቀፍ ሽብርተኝነት የሚያስፈርጁት ሌሎች መመዘኛዎች መሆናቸውን አብራርተዋል።

የትህነግ ቡድን በሚፈፅመው ድርጊት በአለም አቀፍ ሽብርኛ የሚያስፈርጀው ቢሆንም ምዕራባውያን በዝምታ ማለፋቸው በኢትዮጵያ ላይ የያዙትን አቋም በግልፅ ያሳየ መሆኑንም አንስተዋል።

ቡድኑ እየፈፀማቸው ያሉ ወንጀሎችን በመረጃ በማስደገፍ አለም አቀፍ ሽብርተኛ መሆኑን ለአለም ማህበረሰብ ማሳወቅ ደግሞ ከመንግስትና ከህብረተሰቡ የሚጠበቅ ኃላፊነት ነው ሲሉ ምሁራኑ ተናግረዋል፡፡

በተስፋዬ መሬሳ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.