Fana: At a Speed of Life!

በሀዲያ ዞን መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና የወሰዱ የሚሊሻ አባላት ተመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 28 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀዲያ ዞን መሠረታዊ የውትድርና ስልጠና ሲከታተሉ የቆዩ ምልምል የሚሊሻ አባላት በዛሬው ዕለት ተመርቀዋል፡፡
 
በምረቃ ስነ ስርዓቱ ላይ የተገኙት የሀዲያ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማቴዎስ ሎምበሶ÷ ኢትዮጵያ ህዝቦቿ ሰላም ወዳድ በመሆናቸው አንድም ቀን ጦርነት ፈልጋ አታውቅም ብለዋል፡፡
 
ይሁን እንጂ በህልውናዋ ላይ የሚመጡ ኃይሎችን በህዝቦቿ የተባበረ ክንድ በመመከት ሀገርን ለማዳን ገድል የፈጸመች ሀገር ናት ሲሉም አውስተዋል፡፡
 
ይህንንም በቀደሙት ዘመነ መንግታት በርካታ ሀገራት ኢትዮጵያን ቅኝ ለመግዛት አስበው ያልተሳካላቸው አፍሪካዊት ቀንድ ሉአላዊት ሀገር መሆኗን ታሪክ ያመላክተናል ነው ያሉት፡፡
 
በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የገጠማትንን ፈተና በተባበረ ክንድ በመመከት ሠላሟን ለመመለስ የሀዲያ ዞንና ህዝብ በተለያዩ ተግባራት የድርሻውን ሲወጣ መቆየቱን ጠቁመዋል።
 
ከዚህም አንዱ በሆነውና ሀገራዊ ጥሪ ተቀብለው የድርሻቸውን ለመወጣት የተዘጋጁ የዕለቱ ተመራቂ ምልምል የሚሊሻ አባላትን የዚህ ታሪክ ተጋሪ ናቸው ብለዋል።
 
የሀዲያ ዞን ሚሊሻ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ወንድሙ አንሴ በበኩላቸው÷ ምልምል የሚሊሻ አባላቱ በቆይታቸው በሀገራዊ ወቅታዊ ሁኔታ፣ በህገወጥ መሣሪያ ዝውውርና ኮንትሮባንድ ቁጥጥር እንዲሁም መሠረታዊ ወታደራዊ የንድፈ ሀሳብና የመስክ ላይ የተግባር ስልጠና ዕውቀት መቅሰማቸውን ተናግረዋል ።
 
ሰልጣኞቹም በሞራል፣ በከፍተኛ ፍላጎትና ተነሳሽነት ከመሰልጠናቸውም በላይ ለማንኛውም ሀገራዊ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ጠቁመዋል።
 
ምልምሎቹ በስልጠናው ቆይታቸው 70ሺህ 4መቶ ብር በማሰባሰብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ ማድረጋቸውን ከዞኑ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
 
 
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.