Fana: At a Speed of Life!

በፈጠራ ስራዎች ላይ የተሰማሩ ወጣቶች እውቅና ተሰጣቸው

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 28፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ የፈጠራ ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ወጣቶች እውቅና ተሰጥቷቸዋል።
ወጣቶቹ “ትፍጠር ኢትዮጵያ” በሚል መጠሪያ ስር በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና መንግስታዊ ባልሆኑ አጋር ድርጅቶች ድጋፍ ሲደረግላቸው የቆዩ ናቸው።
የፈጠራ ባለሙያዎቹ “ለኮቪድ-19 አገር በቀል መፍትሄ” በሚል መሪ ሃሳብ ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያግዙ የተለያዩ ቴክኖለጂዎችን አበልጽገዋል፡፡
ወጣቶቹ የኤክስሬይ የኮቪድ መመርመሪያ ስካነር፣ ከንክኪ ነፃ የሆኑ የእጅ መታጠቢያዎች፣ ለሆስፒታልና ለሆቴል ክፍሎች የሚገጠሙ አየርን ከብክለት የሚያፀዱ ማሽኖች፣ ሜካኒካል ቬንትሌተርና ሌሎች የፈጠራ ስራዎችን አበረክተዋል።
የመድኃኒቶች አጠቃቀምና ሌሎች መረጃዎችን የያዙ የኦን ላይን ድረ-ገፆች፣ በመኪና ላይ የሚገጠሙ የተሽከርካሪውን የጉዞ ሁኔታ መቆጣጠርና ኮንትሮባንድን ለመከላከል የሚያግዙ ፈጠራዎችም ይገኙበታል።
በእውቅና መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ መንግስት አገር በቀል ፈጠራን ለማበረታታት ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በተለይም ኮቪድ-19 አገር ውስጥ መግባቱን ተከትሎ በተወሰዱ ጠንካራና ቀጣይነት ያላቸው ጥረቶች ውጤት መገኘቱንም ገልጸዋል።
የፈጠራ ባለሙያዎቹ የሰሯቸው ቴክኖሎጂዎች ችግሮችን በአገር ውስጥ እውቀት መፍታት የሚያስችሉና የሚበረታቱ መሆናቸውን መጥቀሳቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.