Fana: At a Speed of Life!

በሰሜን ወሎ ሰርጎ የገባው የህወሓት አሸባሪ ሃይል በመከላከያ ሰራዊት አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሰሜን ወሎ በኩል ሰርጎ የገባው ወራሪው የህወሓት አሸባሪ ሃይል በጀግናው መከላከያ ሰራዊት አፀፋዊ እርምጃ ተወሰደበት ፡፡

በዚህ ስምሪት 142 የሽብር ቡድኑ ታጣቂ ሃይል ሲደመሰስ 4 ስናይፕር ፣ 6 የሞርታር ቅንቡላ ፣ 1 ብሬን ፣ 18 የእጅ ቦምብ ፣ 15 ክላሽ ፣ 7 ሺህ የብሬን ጥይት ፣ 5 ሺህ የክላሽ ጥይት ፣ 1 የመገናኛ ሬዲዬ (1187 አይኮም) ፣ 1 የዋይፋይ ሪሲቨር ፣ 6 የብሬን ሻንጣና 10 የነፍስ ወከፍ ወታደራዊ የወገብ ሻንጣ ከጠላት ሃይል ተማርኳል።

ከግንባሩ አመራሮች መካከል የክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል እንደተናገሩት ፥ ጠላት አሁን ላይ በሰራዊቱ እየደረሰበት ባለው ኪሳራና ባጋጠመው ሽንፈት የተስፋ መቁረጥ እንቅስቃሴዎችን እያደረገ ነው።

ይሁን እንጅ ከገባበት መግደያ ወረዳ መውጣት እንደማይቻለው ጠቅሰው፥ ወራሪውን ሃይል በገባበት በማስቀረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ለህዝቡ የድል ዜና እናሰማለን ማለታቸውን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል ።

በግዳጅ ቀጠናው የብርጌድ ዋና አዛዥ በበኩላቸው በጭፍን ሃገራዊ ጥላቻ ተነሳስቶ የማይሞከረውን መከላከያ ሰራዊት በመፃረር ህዝብን የተዳፈረው አሸባሪ የትህነግ ቡድን በፈፀመው ስህተት የእጁን እያገኘ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።

ሰራዊቱ በተሰለፈበት የወሎ ግንባር በሰርጎ ገቡ ሽብርተኛ ቡድን ላይ እየወሰደ ያለው አሁናዊ እርምጃና በጠላት በኩል የሚስተዋለው መፍረክረክ የፍፃሜውን መቃረብ የሚያመላክት መሆኑም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.