Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያጋጠማትን ፈተና በብልሃትና አንድነት ማለፍ ይገባል – ጠ/ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የሰላም ማስከበር ማዕከል የሁርሶ የኮንቲጀንት ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በመሠረታዊ ወታደርነት ያሰለጠናቸውን ምልምል አባላት አስመረቀ።

በምርቃት ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን የሚጠላ እና ራስ ወዳድ ቡድን መሆኑን ተናግረዋል።

አሸባሪው ህወሓት ለኢትዮጵያ እንቅርት ሆኖባታልም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

ኢትዮጵያ ፈተና ላይ መሆኗን በማንሳትም ይህን ፈተና በብልሃትና አንድነት ማለፍ እንደሚገባና ለዚህም ቆራጥነት እንደሚያስፈልግ አጽንኦት ሰጥተዋል።

አሸባሪው ህወሓት ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እና አንድነቷን ለመበተን እየሰራ ቢሆንም በተቃራኒው ኢትዮጵያ ዳግም አንድ እንድትሆን አድርጓታልም ብለዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሀኑ ጁላ በበኩላቸው የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ዛሬ ሰልጥናችሁ በመመረቃቻሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ ላይ የተደቀነውን ፈተና አለንልሽ ለማለት ስለቆማችሁ እናመሰግናለን ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ፥ ተመራቂዎቹ የኢትዮጵያ ጠላት የሆነውን ህወሓት ለመመከት ስለምትቀላቀሉ ትልቅ ምስጋና አለን ብለዋል።

እራሱን እየሰዋ ያለውን የኢትዮጵያን የቁርጥ ቀን ልጆች ለመቀላቀለል ስለወሰናችሁ እንኳን ደስ አላችሁም ነው ያሉት ጄኔራል ብርሃኑ።

ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ተወጣጥተው በመሰልጠን ዛሬ የተመረቁት ምልምል አባላት በስልጠና ቆይታቸው ዘመናዊ ንድፈ ሀሳብ በተግባር የተደገፈ ወታደራዊ የሙያ ትምህርት ተከታትለዋል።

በ1972 ዓ.ም. በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል የተመሠረተው የሁርሶ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት ለሀገር ሉአላዊነት መረጋገጥ ና ለአለም ሰላም መከበር አስተዋጽኦ ያበረከቱና በማበርከት ላይ የሚገኙ የሠራዊት አባላት ያፈራ አንጋፋ ተቋም ነው።

በቅድስት ተስፋዬ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.