Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 5 የቀበሌ መታወቂያና 25 የባንክ ደብተሮች የተገኘበት ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ አምስት የቀበሌ መታወቂያና 25 የተለያዩ የባንክ ደብተሮች ይዞ ሲንቀሳቀስ የነበረን ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

አቶ ማሃሪ ተከስተ ገብረኪዳን የተባለው ግለሰብ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ናሆም አደባባይ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፥ ምርመራ እየተካሄደበት እንደሚገኝ የፀጥታና ህግ-ማስከበር የቀጠና 1 ሻለቃ 2 ኃይል 1 አዛዥ ኢንስፔክተር አዲሱ ተሾመ ገልፀዋል፡፡

አሁን ያለውን ወቅታዊ የፀጥታ ችግር የአሸባሪው ህወሓት ጁንታ ቡድን በተለያዩ ቦታዎች ጥቃት ለመፈፀም የተለያዩ ሰዎችን እየተጠቀመ መሆኑንም ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻርም የሽብር ቡድኑን ተግባር ለማስፈፀም የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ስላሉ የፌደራል ፖሊስ ከአዲስ አበባ ፖሊስ ጋር በመቀናጀት ጠንካራ ፍተሻ እያደረገ እንደሚገኝም ነው የተናገሩት።

ግለሰቡ በያዛቸው የባንክ ደብተሮች ውስጥ 2 ሚሊየን 966 ሺህ 189 ብር እንደተገኘበት የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያመላክታል።

ህብረተሰቡም ፀጉረ ልውጦችን በሚያይበት ጊዜ ለፀጥታ አካላት ሪፖርት እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.