Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል መስሪያ ቤቶች በወሎ ግንባር ለሰራዊቱ 135 ሰንጋዎችና 42 በጎችን ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል መስሪያ ቤቶች የመንግስት ሰራተኞች ከወር ደመወዛቸው በመስጠት እና ከሌሎች ህብረተሰብ ክፍል 135 ሰንጋዎችንና 42 በጎችን ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለልዩ ሃይል እና ለሚሊሻው ድጋፍ አድርገዋል፡፡
 
ድጋፉን ያስረከቡት የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳደር አማካሪ አቶ አሚን ጁንድ ድጋፉ የአሸባሪው ቡድን እስከሚጠፋ ድረስ ይቀጥላል ብለዋል፡፡
 
አሸባሪው ህወሓት የአማራ እና የኦሮሞ ህዝብን ለመከፍፈል ቢሰራም ሁለቱ ወንድማማቾች የጋራ ጠላታቸውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያጠፉታል ነው ያሉት፡፡
 
የመከላከያ ሰራዊት ተወካይም የአሸባሪው ቡድን በአሁኑ ወቅት በሁሉም ግንባሮች እየተደመሰሰ ነው ብለዋል፡፡
 
ሰራዊቱ በርካታ ድሎችን እያስመዘገበ ነው ያሉት ተወካዮ የህዝባችንን ድጋፍ ይዘን የሽብር ቡድኑን እንቀብረዋለን ማለታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል፡፡
 
የኦሮሚያ ክልል እስካሁን ድረስ 263 ሚሊዮን ብር የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.