Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ኮሌጆች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች አስመረቁ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋርማ ኮሌጅ እና ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለየዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቀዋል፡፡

ፋርማ ኮሌጅ 559 ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ከነዚህ መካከልም 359 የሚሆኑት በመጀመሪያ ዲግሪና በደረጃ የተመረቁ ናቸው።

200 ተማሪዎች ደግሞ በሁለተኛ ዲግሪ መመረቃቸውን የፋርማ ኮሌጅ ሬጅስትራር ሃላፊ ወይዘሮ ሜላት ስዩም ተናግረዋል።

የፋርማ ኮሌጅ ፕሬዚዳንት አቶ ስዩም ከበደ ዛሬ የተመረቁ ተማሪዎች በሰለጠኑበት ሙያ ሀገራቸውንና ህዝባቸውን በቅንነትና በታማኝነት ማገልገል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በተመሳሳይ ጠዳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ለ15ኛ ጊዜ በስድስት የሙያ ዘርፎች በመካከለኛ ደረጃ 564 የጤና ባለሙያዎች ዛሬ አስመርቋል፡፡

የኮሌጁ ዲን አቶ ዘመነ ኮሌጁ በመካከለኛ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን እያስመረቀ በጤናው ዘርፍ ብቁ የሰው ሀይል እያፈራ ነው ብለዋል።

ኮሌጁ ለ15ኛ ጊዜ በዛሬው ዕለት 564 የጤና ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን÷ ከዚህ ውስጥ 350ዎቹ ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ኮሌጁ በማህበራዊ ዘርፍ በርካታ ተግባራት ከውኗል ያሉት አቶ ዘመነ÷ በህልውና ዘመቻው የጤና ባለሙያዎችን ግንባር ድረስ በመላክና ልዩ ልዩ ድጋፎችን ማድረጉን አንስተዋል።

በምናለ አየነው እና ጥላሁን ይልማ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.