Fana: At a Speed of Life!

በመዲናዋ 108 የመገበያያ ቦታዎችናተጨማሪ የግብርና ምርት ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ 108 የመገበያያ ቦታዎችን እና ከ250 ሺህ ኩንታል በላይ ተጨማሪ የግብርና ምርት መዘጋጀቱን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ የጀመሩት መሸጫዎቹ በከተማችን የሚስተዋለውን የኑሮ ውድነት በማረጋጋት በተለይም የግብርና ውጤት የሆኑ የሰብል፣ የአትክልትና ፍራፍሬ ምርቶችን እንዲሁም እንደ እንቁላል ያሉ የእንስሳ ተዋጽኦ አቅርቦትን ይበጥል በማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖራቸዋል።

በዚህም 56 የቁም እንሰሳት መገበያያ እንዲሁም 52 የአትክልትና ፍራፍሬ መሸጫዎች በሁሉም ክፍለ ከተሞች ስራ መጀመራቸውን ምክትል ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ አስፍረዋል፡፡

መሸጫ ማዕከላቱ ለሸማቹ ህብረተሰብ ምርት በቀጥታ ከአርሶ አደሩ ማሳ ከማቅረባቸው በተጨማሪ ምርቶቻቸውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረባቸው ተመራጭ ያደርጋቸዋል ነው ያሉት፡፡

በቀጣይም መሰል አቅርቦቶችን የማሟላቱ ጥረት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.