Fana: At a Speed of Life!

የከተማና ገጠር መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ችግሮችን ለመቅረፍ በቅንጅትይሰራል-አቶ ሽመልስ

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በከተማና በገጠር የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር የሚስተዋሉ ችግሮቹን ለመቅረፍ በትኩረት እንደሚሰራ የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ዙሪያ ለአስር ቀናት በአዳማ ከተማ ሲካሄድ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።

በመድረኩ ንገግር ያደረጉት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ 2014 በጀት ዓመት በከተማና በገጠር የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ጉዳዮች ላይ ችግር የሚፈጥሩ አመራሮች ተጠያቂ ይደረጋሉ ብለዋል፡፡

መሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ቢሮ ሃላፊ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ በበኩላቸው÷ ቢሮዉ በ2014 ዓ.ም የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርዓትንና አገልግሎት አሰጣጥን ለማዘመን እየሰራ እንደሚገኝ ጠቁመዋል።

ስልጠናው በመሬት አስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚሰሩ የክልል፣የዞን፣የወረዳና የከተማ አስተዳደር አካላት አቅም የሚገነባና በክልሉ ያሉ የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት እንደሚያግዝ መገለጹን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.