Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ስንቅ ለህልውና ዘመቻው ተዘጋጅቷል

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጎንደር ከተማ በሴቶች አደረጃጀት ግምቱ ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ስንቅ ለህልውና ዘመቻው መዘጋጀቱን የከተማ አስተዳደሩ ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ አስታውቀዋል።
 
የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ወይዘሪት ትዕግሥት ገዳሙ÷ በህልውና ዘመቻው ለሚፋለሙ የፀጥታ አካላት በከተማ ደረጃ በሴቶች አደረጃጀት ምግብነክ የሆነ ያልሆነ ስንቅ እየተዘጋጀ ነው ብለዋል።
 
በስድስቱ ክፍለከተሞች 1ሺህ 600 ኩንታል ዳቦ ቆሎ በሶ ቆሎ ኩኪስና ሌሎች የምግብ አይነቶች ከህብረተሰቡ በተፈጠረው አደረጃጀት ተዘጋጅቷል ነው ያሉት።
 
እስከአሁን የተሰበሰበውና የተዘጋጀው ስንቅ ወደ ገንዘብ ሲቀየር ግምቱ 17ሚሊየን 033 ሺህ 714 መሆኑን ምክትል መምሪያ ሃላፊዋ ገልጸዋል።
የከተማው ህዝብ በስንቅ ዝግጅቱ እያደረገ ያለው ተሳትፎ እያደገ መጧል ያሉት ሃላፊዋ ከዕቅዱ አንፃር ግን በሚፈለገው ደረጃ አለመሆኑን ተናግረዋል።
 
ወደ ግንባር ከተዘጋጀው ስንቅ መላኩን ያስታወሱት ሃላፊዋ ለዘመቻ ቤተሰቦችም ድጋፍ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል።
 
በምናለ አየነው
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.