Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፓራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን አዲስ አበባ ሲገባ አቀባበል ተደረገለት

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቶኪዮ 2020 ራሊምፒክ ጨዋታ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
 
የኢትዮጵያ ራሊምፒክ ብሔራዊ ቡድን በ3 አትሌቶች የተወከለ ሲሆን 1 ወርቅ ሜዳሊያ እና 2 ዲፕሎማ በማግኘት ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ ውድድሩን አጠናቋል፡፡
 
ብሔራዊ ቡድኑ ዛሬ ከማለዳው 1:00 ሰዓት ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
 
በአቀባበሉ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ እና የስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኤሊያስ ሽኩርን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ከስፖርት ኮሚሽን  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.