Fana: At a Speed of Life!

በህወሓት ወረራ ምክንያት የተፈናቀሉ ዜጎችን ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሐሴ 29 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጦርነት ምክንያት ሐብት ንብረታቸው የወደመባቸውን ዜጎች ለመደገፍ እና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም በጎንደር ዩንቨርሲቲ አዘጋጅነት በጎንደር ከተማ ውይይት እየተካሄደ ነው።
 
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አማካሪ አቶ ደሳለኝ አስራደ÷ ህውሓት በሀገራችን ላይ እያደረሰ ያለው ግፍ ታሪክ የማይሽረው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
 
ወረራውን ሃይል ለመመከትም በጋራ የምንሰራበት እና አሸባሪውን እስከመጨረሻው የምንደመስስበት ወቅት አሁን ነው ብለዋል።
 
የምዕራቡ ዓለም ከአሸባሪው ጎን በመሆን ኢትዮጵያን ሊያፈርሱ ቢጥሩም አይሳካላቸውም፤ ለዚህ ደግሞ ልጆቿ ታሪክ ይሰራሉ ነው ያሉት።
 
የጎንደር ከተማ ከንቲባ አቶ ሞላ መልካሙ በበኩላቸው÷ የህውሓት አሸባሪ ቡድን አማራን ማዳከም እና ኢትዮጵያን ማፍረስ ዛሬ የጀመረው ተግባር እንዳልሆነ ገልጸዋል፡፡
 
በአማራ እና አፋር ክልል እያደረሰ ያለውን ግፍ ለማስቆም ሁሉም ዜጋ አንድ በመሆን መዋጋት እንዳለበት አሳስበዋል።
 
በቁስ እና በሰው ልጅ ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ከባድ ቢሆንም ስነ ልቦናችንን ስላልሰበረ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሰን በመገንባት ጥንካሬያችንን ማሳየት ይኖርብናል ብለዋል።
 
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ፕርዚዳንት ዶ/ር አስራት አፀደወይን ÷ የአሸባሪ ቡድኑ በአማራ ክልል እያደረሰ ያለው መንግስታዊ ተቋማትን የማውደም ስራ ሀገር ጠል መሆኑን እና ተስፋ መቁረጡን የሚያሳይ ሲሆን በሰብዓዊ መብት ጥሰቱ ደግሞ አረመኔያዊ አስተሳሰቡን ያሳያል ብለዋል።
 
በመሆኑም ይሄ አሸባሪ ቡድን የሚሰራቸውን ግፎች እንዲያቆም በጋራ መስራት ይኖርብናል ፤ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ በማድረግ እና በግንባር የሚዋደቁትን ወንድሞቻችንን በሎጅስክ በማገዝ ኢትዮጵያን ማዳን ይገባናል ብለዋል።
 
በመድረኩ ህውሓት ያደረሳቸውን እና እያደረሰ ያለውን ጉዳት በቦታው ተገኝተው ጥናት ያደረጉ ባለሙያዎች ፅሁፍ አቅርበዋል።
በስንታየሁ አራጌ
 
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.