Fana: At a Speed of Life!

በደብረዘቢጥ የነበረው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተደመሰሰ

በደብረዘቢጥ ሰርጎ የገባው የአሸባሪው ህወሓት ቡድን ተደመሰሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በጋይንት ግንባር ሰርጎ የገባው የህወሓት የሽብር ቡድን እየተደመሰሰ መሆኑን የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አስታወቀ፡፡

የሰሜን ምዕራብ ዕዝ አንደኛ ኮር አዛዥ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁት÷ የህወሓት የሽብር ቡድን መሽጎበት ከነበረው ከደብረ ዘቢጥ ዋሻ ሙሉ በሙሉ ተደምስሷል፡፡

በውጊያውም የሽብር ቡድኑ አዋጊ ከፍተኛ መኮንኖች መደምሰሳቸውንም ገልፀዋል፡፡

የአዋጊዎቹ ማንነት እንዳይታወቅም አንገታቸውን እየቆረጡ ጥለው መሄዳቸውንም ነው የተናገሩት፡፡

ከሞት የተረፉትም ከፍተኛ የሰብዓዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ደርሶባቸው ከጋይንት አካባቢ ዘርፈውት የነበረውን ንብረት እየጣሉ ወደ አግሪት እና ፍላቂት መሸሻቸውን ጀኔራሉ አስረድተዋል፡፡

ከነበረበት ደብረ ዘቢጥ ወደ ሰሜን ወሎ አግሪት እና ፍላቂት በመሸሽ ላይ ያለውን ቡድን ሙሉ በሙሉ ለመደምሰስ መከላከያ ሰራዊት፣ ልዩ ኃይል፣ ሚሊሻ እና የአካባቢው ነዋሪዎች በሎጅስቲክስ እንዲሁም በውጊያ ተባብረው እየሰሩ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

የደቡብ ጎንደር ዞን አስተዳዳሪ አቶ ቀለመወርቅ ምህረቴ በደብረ ዘቢጥ ግንባር ተገኝተው የፀጥታ አካላትን እና የሰሜን ወሎ አመራሮች ህብረተሰቡን እንዲያንቀሳቅሱም አበረታተዋል፡፡

በምንይችል አዘዘው እና ዙፋን ካሳሁን

ፎቶ – አሚኮ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.