Fana: At a Speed of Life!

ህወሓት በአፋር ባደረሰው ጉዳት ለተፈናቀሉ ወገኖች ጂማ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው የህወሓት ቡድን በአፋር አካባቢዎች በከፈተው ጦርነት ምክንያት ለተፈናቀሉ ወገኖች ጂማ ዩኒቨርሲቲ የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

የአፋር ክልልን ከትግራይ ክልል በሚያዋስናቸው የአፋር አካባቢዎች አሸባሪው የህወሓት ቡድን በከፈተው ጦርነት ምክንያት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በተለያዩ አካባቢዎች ለተጠለሉ ዜጎች የቁሳቁስ ድጋፍ እንዲደረግ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ባቀረበው ጥሪ መሰረት ጂማ ዩኒቨርሲቲ ድጋፍ ማድጉን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል፡፡

በዚህም በድምሩ 2 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር የሚያወጡ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን÷ ድጋፉም ፍራሽ፣ አልባሳት፣ የቤት ቁሳቁስ፣ ምግብ እና ምግብ ነክ መሆናቸውን ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.