Fana: At a Speed of Life!

የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲያደርጉ የነበሩትን ውይይት የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀቁ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሲያደርጉ የነበሩትን ውይይት የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት አጠናቀዋል፡፡

ፓርቲዎቹ የቀረቡትን የውይይት መነሻ ጽሁፎችን ገምግሞ አስተያየት ከሰጡ በኋላ በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ የሚከተሉትን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ተገዳ የገባችበትን ጦርነት ከውጪ ጠላትና ከውስጥ ባንዳ የተቃጣብንን የሉዓላዊነት ጦርነት ለመመከት ፓርቲዎች መንግስት በጠራው ስብሰባ ላይ ተገኝተው በጥልቅ መክረዋል፡፡

መንግስት በልበ-ሰፊነት አይቶ ያደረገውን የተናጠል ተኩስ አቁም እየደገፍን በሃገራችን ላ የተቃጣውን ጦርነት ሁለንታዊ ድጋፍ የምናደርግ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

የእናት ጡት ነካሽ የሆኑት አሸባሪው ህወሓት እና የእንጀራ ልጁ ሸኔ በህዝባችን እና በሃገራችን የከፈቱትን ጦርነት በጽኑ እናወግዛለን፡፡

የሃገራችን ሉዓላዊናት ለማስከበር ከሃገር መከላከያ ሰራዊትና ከክልል ልዩ ሃይሎች ጋር አብረን በመሆን ለሃገራችን እንዘምታለን፡፡
ምዕራባውያን የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ለመነዳፈር በእጅ አዙር የሚያደርጉት ጦርነት በአስቸኳይ አቁመው ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር እንዲቆሙ ጥሪ እናቀርባለን፡፡

የአፍሪካ ህብረት ጎረቤት ሃገር ሱዳን እና ግብጽ በሃገራችን በኢትዮጵያ ላይ የሚፈጽሙትን ደባ እና ሴራ እንዲሁም የሚዳፈሩትን ሉዓላዊነት እንዲያቆሙ እንዲያደርግ ድርጅቱን በአጽንዖት እየጠየቅን፣ የኢጋድ አባላ ሃገሮችም በሃገራችን ኢትዮጵያ እየተሰነዘረ ያለውን ወንጀልና የስም ማጥፋት ዘመቻ እንዲያስቆሙልን፤ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን እንዲቆሙ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በሃገራችን እየታየ ያለውን የዋጋ ንረት እና የሃሰት ፕሮፓጋንዳ የሚያሰራጩ ሚዲያዎችና ግለሰቦችን መንግስት ጥብቅ ቁጥጥር አድርጎ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወስድ እንጠይቃለን፡፡

በችግራችን ጊዜ ከኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት የተሰለፋችሁ ወዳጅ ሃገራት፣ ህዝብና መንግስታት፣ ዓለም አቀፍ በጎ አድራጎት ድርጅቶች እስካሁን ላደረጋችሁልን ድጋፍ ምስጋና እያቀረብን ወደፊትም የተለመደ ትብብራችሁን እና ድጋፋችሁ እንዳለየን እንጠይቃለን፡፡

ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ የተቃጣብንን ወረራ እና ጥቃት የተለመደውን የአባቶቻችን ጀግንነትና ወኔ የተላበሰው መከላከያ ሰራዊታችን እና የክልል ልዩ ሃይሎችን አኩሪ ድል እየተቀዳጁና የክብር መስዋዕት እየከፈሉ ጠላትን በማሳደድ ላይ ይገኛሉ፡፡

በመሆኑም ከአብራክህ የተከፈሉ ልጆችህን ለመርዳት እና ጋሻ ለመሆን ያሳየኽው አኩሪ ታሪክ እንደተጠበቀ ሆኖ አሁንም የሃገራችን ሰላም እስኪረጋገጥ የጋራ ክንዳችንን በጋራ ለጋራ በማነሳሳት አለኝታ መሆናችንን የምናሳይበት ወቅት በመሆኑ ከጫፍ እከ ጫፍ ድንበራችንን እንድንጠብቅ፣ የአካባቢያችንን ሰላም እንድንቆጣጠር በታላቅ አክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

በአዲሱ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.