Fana: At a Speed of Life!

ከትርፍ ይልቅ ሃገርና ሕዝብን ያስቀደሙ የግል ትምህርት ቤቶችን ማመስገን ያሻል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለመጪው የ2014 የትምህርት ዘመን ወርሃዊ ክፍያ ጭማሪ ባለማድረግ ከትርፍ ይልቅ ሃገርና ሕዝብን ያስቀደሙ የግል ትምህርት ቤቶች ሊመሰገኑ እንደሚገባ ተጠቆመ።

የክፍያ ጭማሪ ካላደረጉት ትምህርት ቤቶች መካከል የማቪዝ አጸደ ህጻናትና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር አቶ በቀለ ቶሌራ ሃገር ያለችበት ሁኔታ ትርፍ የሚታሰብበት አለመሆኑን ገልጸዋል።

በጦርነቱ ምክንያት በምጣኔ ሃብቱ ላይ የደረሰውን ጫና ታሳቢ በማድረግ ከትርፍ ይልቅ ሃገርና ሕዝብን በማስቀደም በ2014 የትምህርት ዘመን የክፍያ ጭማሪ ላለማድረግ መወሰናቸውን ተናግረዋል።

ሃገር የተደቀነባትን የሉዓላዊነት ፈተና ለማለፍ ለሃገሩ ሁሉም ጦር ግንባር ባይዘምትም በተሰማራበት የስራ ዘርፍ ለኅብረተሰቡ ወቅቱን ያገናዘበ አገልግሎት መስጠት ተገቢ ነው ብለዋል።

ልጆቻቸውን በትምህርት ቤቱ የሚያስተምሩ ወላጆችም ትምህርት ቤቱ ሃገር ያለችበትን ፈታኝ ወቅትና የኑሮ ውድነት ከግምት በማስገባት የክፍያ ጭማሪ ባለማድረጉ አመስግነዋል።

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱም “አሁን ያለንበት ነባራዊ ሁኔታ በመተሳሰብና በመደጋገፍ የምንሻገረው እንጂ አንዱ በአንዱ ላይ ተንጠላጥሎ የሚያልፍበት አይደለም” ብለዋል።

በከተማዋ ከሚገኙ ከ1 ሺህ 700 በላይ የግል ትምህርት ቤቶች መካከል 700ዎቹ ለ2014 የትምህርት ዘመን ጭማሪ አለማድረጋቸውን በመግለጽ ምስጋና ማቅረባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.