Fana: At a Speed of Life!

የተለያዩ ተቋማት በአሸባሪው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት በአፋር ክልል በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች ከፍኛ የትምህርት ተቋማት እና የንግድ ተቋማት በጥሬ ገንዘብና በዓይነት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
በዚህም የአፋር ጨው አምራቾች አክሲዮን ማህበር 2 ሚሊየን ብር ሲለግስ የሰመራ፣ ሐረማያ፣ ወለጋ፣ ቦንጋ፣ ዋቸሞ እና ቡሌሆራ ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ 11 ነጥብ 1 ሚሊየን ብር የሚገመት ምግብ ነክ፣ የመገልገያ ቁሳቁስ፣ ብርድ ልብሶችና ፍራሾችን አበርክተዋል፡፡
የአፋር ጨው አምራቾች አክሲዮን ማህበር ተወካይ ኢንጂነር መሐመድ ያሲን ማህበራቸው በአሸባሪው ቡድን ወረራ የተፈናቀሉ ወገኖች እስኪቋቋሙ ድጋፉን እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡
የአፋር ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አሸባሪው ህወሓት በፈጸመው ወረራ ለተፈናቀሉ ወገኖች እንዲውል ማህበሩና ዩኒቨርሲቲዎቹ ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
ለተፈናቃዮች ተመሳሳይ ድጋፍ እንዲያደርጉ ርዕሰ መስተዳድሩ ጠይቀዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.