Fana: At a Speed of Life!

የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ይፈጸማል

አዲስ አበባ፤ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የድምፃዊ አለማየሁ እሸቴ ሥርዓተ ቀብር የፊታችን ማክሰኞ ጳጉሜን 2 ቀን 2013 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸም የአርቲስቱ የቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ አስታወቀ።

የአርቲስቱ የአስክሬን ሽኝት በመስቀል አደባባይ እንደሚከናወንም ተገልጿል።

አርቲስት አለማየሁ እሸቴ ከትናንት በስቲያ ነሐሴ 27 ቀን 2013 ባደረበት የልብ ሕመም በ80 ዓመቱ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።

የኮሚቴው አባል የሙዚቃ ባለሙያ ዳዊት ይፍሩ የአርቲስቱን የቀብር ሥነ-ሥርዓት እንዲያስተባብር የተቋቋመው ኮሚቴ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት፣ ከአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤትና ከኢትዮጵያ የሙዚቃ ዘርፎች ማኅበራት ሕብረት መዋቀሩን ገልጿል።

የአርቲስት አለማየሁ እሸቴ የቀብር ስነ ሥርዓት ጳጉሜን 2 ቀን 2013 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እንደሚፈጸምና ከሥርዓተ ቀብሩ በፊት በመስቀል አደባባይ ሽኝት እንደሚካሄድና መርሃ ግብሩ ከረፋዱ 5 ሠዓት እስከ ቀኑ ዘጠኝ ሠዓት ድረስ እንደሚቆይ አስታውቋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.