Fana: At a Speed of Life!

አራቱ ወንድማማች የኢትዮጵያ ዘማቾች

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) አራቱ የጋሽ ኑር ልጆች እኛ እያለን ሀገር አትፈርስም ብለው ብርሸለቆ ማሰልጠኛ ገብተው ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ነው፡፡

ዘማች ወንድማማቾቹም ቃሲም ኑር፣ ኤዳሶ ኑር፣ ታጁ ኑር እና ዘይኑ ኑር ይባላሉ።

አራቱ ወንድማማቾች ጁንታው ሀገር ሊበትን ቢያስብም እኛ የኢትዮጵያ ልጆች እያለን ይህ እንዴት ይሆናል ብለው ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በአንድነት መዝመት እንዳለባቸው መክረው ስልጠናቸውን በሚገባ እየተከታተሉ እንደሚገኙ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

አባታቸው ጋሽ ኑር 11 ወንድ ልጆች እና 6 ሴት ልጆች አሏቸው።

ወደማሰልጠኛው የገቡት አራቱ ወንድማማቾች “አባታችን በሀገር ፍቅር ስሜት እና ወኔ ነው አንጾ ያሳደገን÷ በዚህም ምክንያት አገር ጥሪ ስታቀርብ መርቆና በአባገዳዎች አስመርቆ ሸኝቶናል” ነው ያሉት።

“ጁንታውን ሳንቀብር ደግሞ ወደቤታችን አንመለስም” ብለዋል ወንድማማቾቹ።

ወንድማማቾቹ ሀገር አፈርሳለሁ ብሎ የመጣ እራሱ ይፈርሳል እንጂ÷ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጸንታ ትኖራለች የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.