Fana: At a Speed of Life!

የማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴን ለማሳደግ ብዙ መስራት እንደሚገባ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳትፎ የበለጠ እንዲያድግ ብዙ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ።

የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን የ2013 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርትና የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ውይይት አካሂዷል።

የማህበረሰብ ስፖርት÷ የህብረተሰቡ ጤና በመጠበቅ፣ አገሪቷ ለመድሐኒት የምታወጣውን የውጪ ምንዛሬ መጠን በመቀነስ፣ የእርስ በእርስ ትስስር በመጨመርና ወጣቶች አልባሌ ቦታ እንዳይውሉ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ሚና የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ገልጸዋል፡፡
በኢትዮጵያ በመንግስት ደረጃ ይህን ለማስፋፋት ሰፋፊ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን ጠቁመው፤ ለዚህ ህብረተሰቡ በተሳትፎ የሰጠው ምላሽ አበረታች መሆኑን ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ አሁንም “የብዙሃን የማህበረሰብ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ተሳታፊዎችን ቁጥር ለማሳደግ ብዙ መስራት ይገባል” ብለዋል።
የውይይቱ ተሳታፊዎችም በሰጡት አስተያየት መንግስት ለማህበረሰብ ስፖርት የሰጠው ትኩረት ያህል እንዳልተሰራ ነው ያስታወቁት።

ለዚህም እንደ ችግር ያስቀመጡት የኮቪድ 19 እና የስፖርት አመራር አባላት የቁርጠኝት ችግር መሆኑን ነው።

የስፖርት ማዘውተሪ ቦታዎች ተጠብቀው እንዲቆዩ የይዞታ ካርታ የሌላቸውን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በማቀናጀት ካርታ እንዲሰራላቸው የማድረግ ትኩረት እንዲሰጠው ተጠይቋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዴየሞች ግንባታ ስራም ትኩረት እንደሚሻ ነው የገለጹት።

አሁን ላይ የባህር ዳር ስታዴየም ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች እንዲያካሂድ የተመረጠ ቢሆንም ሙሉ በሙሉ ያለመጠናቀቁ ተነስቷል።

በመሆኑም የባህር ዳር ስታዴየም ጨምሮ ሌሎች ስታዴየሞች አቅም በፈቀደ ልክ ግንባታው እንዲጠናቀቅ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል ሲል ኤዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.