Fana: At a Speed of Life!

የቤንች ሸኮ ዞን ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው ሶስተኛ ዙር ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የቤንች ሸኮ ዞን ነዋሪዎች ለህልውና ዘመቻው በዓይነት፣ በጥሬ ገንዘብ እና በደም ልገሳ ድጋፍ አደረጉ፡፡

ከገንዘብ እና ደም ልገሳ ባሻገር በመዝመት ጭምር በርካቶች ሰራዊቱን ተቀላቅለዋል።

በዞኑ የሚገኙ ወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለሶስተኛ ዙር ሀብት በማሰባሰብ በዛሬው ዕለት 150 ሰንጋ፣ 72 በግ እና ፍየል፣ 14 ኩንታል በቆሎ ለሠራዊቱ አበርክተዋል፡፡

በሶስተኛው ዙር ለህልውና ዘመቻው የተበረከተው ድጋፍ 13 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ሲሆን÷ በቀጣይ የህልውና ትግሉ ግቡን ይመታ ዘንድ ለሰራዊቱ የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በዘላለም ግድየለው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.