Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ የደን ሽፋኑ 17 በመቶ ደረሰ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ዓመታት በአካባቢ ጥበቃ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገሪቷ የደን ሽፋን 17 በመቶ መድረሱን የአካባቢ ደንና አየር ንብረት ለውጥ ኮሚሽን ገለፀ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር ፍቃዱ በየነ እንደገለፁት ባለፉት ዓመታት በተፈጥሮ ሀብት ልማትና እንክብካቤ ላይ በተሰሩ ስራዎች የሀገራችን የደን ሽፋን 17 በመቶ ደርሷል።

በየጊዜው በተፈጥሮ ሀብት ላይ በሚደርሰው ጉዳት በተለይ የእርሻ መሬት ለማስፋፋት፣ ግጦሽ፣ ሀገ-ወጥ ሰፈራና ምንጣሮ የሀገርቷ የደን ሽፋን ወደ 3 በመቶ ወርዶ እንደነበር አስታውሰዋል።

በ2013 ዓ.ም በተካሄደው የደን ሀብት ቆጠራ ሽፋኑ 17 በመቶ ላይ ደርሷል ያሉት ኮሚሽነሩ አሁን የተገኘው ውጤት ባለፉት ሶስት ዓመታት በአረንጓዴ አሻራ ፕሮግራም የተተከሉትን ችግኞች አያካትትም ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.