Fana: At a Speed of Life!

የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች በማይፀብሪ ግንባር በመገኝት ድጋፍ አደረጉ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 29፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የጎንደር ከተማ ነጋዴዎች በማይፀብሪ ግንባር በመገኝት ግምቱ ከ 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ።
ነጋዴዎች በማይፀብሪ ግንባር አሸባሪውን የህውሓት ሀይል አይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት የሚዋደቁትን የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላትን ለማበረታታትና ደጀን ለመሆን ግንባር ድረስ በመገኝት የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጋቸውን የነጋዴዎቹ ተወካይ አቶ መልኩ ሙሌ ተናግረዋል።
በደባርቅ ዳባትና ወቅን ለሚዋጋው የወገን ሀይል 800 ካርቶን ብስኩት 10ሺህ ዳቦ 21ሺህ እንጀራና ሌሎች ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችን መስጠት መቻሉን ተወካዩ ገልፀዋል።
በተጨማሪም 4ሺህ ቲሸርቶች ለመከላከያ ሰራዊት በስጦታ ማበርከት እንደተቻለ የገለፁት ተወካዩ÷ የንግዱ ማህበረሰብም የበኩሉን መወጣት ስላለበት ሃገራዊ ሀላፊነታችን ተወጥተናል ነው ያሉት።
በከተማዋ በተለያዩ የንግድ ዘርፍ ከተሰማሩ ነጋዴዎች በተወጣጣ ግምቱ ከ2ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ገንዘብ የተለያዩ ለሰራዊቱ የሚያስፈልጉ ድጋፎች ተደርገዋል ነው የተባለው።
ነጋዴዎቹ በቀጣይም የጠላት ሀይል እስኪደመሰስ ድረስ ለህልውና ዘመቻ የሚያደርጉትን ሁሉን ዓቀፍ ድጋፍ እንቀጥላለን ብለዋል።
በምናለ አየነው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.